ለኢትዮጵያ ሱቆች · For Ethiopian shops

ክፍያ ሲገባ
ጮክ ብሎ ይናገራል።

ደንበኛ በtelebirr ወይም በባንክ ሲከፍል፣ ብርቤል ወዲያው በአማርኛ “ብር 450 ከአበበ ገብቷል” ይላል። ስልክዎን ማየት አያስፈልግም፤ የውሸት የክፍያ ስክሪን አያታልልዎትም።

BirrBell announces every telebirr and bank payment out loud, in Amharic — so you never miss one and never get fooled by a fake screenshot.

በ3 ደረጃ ይጀምሩ Start in 3 steps

  1. 1

    አፑን ይጫኑ

    ክፍያ የሚመጣበት ስልክ ላይ ብርቤልን ይጫኑ፣ በስልክ ቁጥርዎ ይግቡ።

    Install on the phone that gets payment SMS. Log in with your number.

  2. 2

    ፈቃድ ይስጡ

    የማሳወቂያ ፈቃድ ይስጡ። ብርቤል የሚያነበው የክፍያ መልዕክቶችን ብቻ ነው።

    Allow notification access. Only payment messages are read.

  3. 3

    ይስሙ

    ከአሁን በኋላ እያንዳንዱ ክፍያ ይነገራል — አፑ ዝግ ቢሆንም።

    Every payment is spoken — even when the app is closed.

ለሱቅዎ የሚያስፈልገው ሁሉ Everything your shop needs

🔊

በአማርኛ ይናገራል

የተቀዳ የአማርኛ ድምፅ። ሙዚቃ ቢከፈትም ድምፁን ቀንሶ ይናገራል።

🛡️

የውሸት ክፍያ የለም

ከትክክለኛው telebirr ወይም ባንክ የመጣ መልዕክት ብቻ ይቆጠራል። የስክሪን ፎቶ አያታልልም።

📒

የዱቤ ደብተር

ማን ምን እንደወሰደ፣ ስንት እንዳለበት። ለደንበኛው በኤስኤምኤስ ማረጋገጫ ይላካል። በ4 ቁጥር ፒን የተጠበቀ።

📊

የቀን ገቢ

ዛሬ፣ በሳምንት፣ በወር የገባ — በtelebirr እና በእያንዳንዱ ባንክ ተለይቶ።

📱

ለካውንተር ስልክ

ክፍያው የሚመጣው ባለቤቱ ስልክ ላይ ቢሆንም፣ ካውንተር ያለው ስልክ ይናገራል።

📶

ያለ ኢንተርኔትም

ክፍያን ለማንበብ እና ለመናገር ኢንተርኔት አያስፈልግም።

ይሰራል፡ telebirr · Bank of Abyssinia · ሌሎች ባንኮች በቅርቡ

ዋጋ · Price

2 ሳምንት ነፃ

ከዚያ በወር ብር 300 ብቻ — በtelebirr በአፑ ውስጥ ይከፍላሉ። ውል የለም፤ ሲፈልጉ ያቆማሉ።

2 weeks free, then 300 birr a month, paid by telebirr inside the app. No contract.

አሁኑኑ ይጀምሩ Get BirrBell

ለAndroid ስልክ (Android 8 እና ከዚያ በላይ)።

ጥያቄዎች FAQ

የግል መልዕክቶቼን ያነባል?

አይ። ብርቤል የሚያየው ከtelebirr እና ከባንኮች የመጣ የክፍያ መልዕክት ብቻ ነው። ሌሎች መልዕክቶች አይቀመጡም፣ አይላኩም።

የtelebirr ፒኔን ይፈልጋል?

በፍፁም። ፒን፣ የይለፍ ቃል ወይም ገንዘብ አይነካም — የገባውን ብቻ ያሳውቃል።

ስልኩ ቢዘጋ ወይም ኢንተርኔት ቢጠፋ?

ክፍያን ማንበብ እና መናገር ያለ ኢንተርኔት ይሰራል። ካውንተር ስልክ ከተገናኘ፣ የመልዕክት ስልኩ ሲጠፋ ያሳውቃል።

ዱቤ ደብተሩ ላይ ያለው መረጃ የት ይቀመጣል?

በስልክዎ ላይ ብቻ፣ በፒን የተጠበቀ።